መዝሙር 82:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በአማልክት ጉባኤ መካከል ተሰየመ፤ በአማልክትም ላይ ይፈርዳል፤ እንዲህም ይላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሳፍ መዝሙር። እግዚአብሔር በመለኮታዊ ጉባኤ ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በሰማያዊው ጉባኤ አማልክት ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፥ በመካከላቸው ተገኝቶ ፍርድ ይሰጣል፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል። |
ነገር ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች ከሕዝቡ ሁሉ ምረጥ፤ እነዚህም ሰዎች እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ታማኞችና በማታለል የሚገኘውን ጥቅም የሚጸየፉ ይሁኑ። የሺሕ፣ የመቶ፣ የዐምሳ፣ የዐሥር፣ አለቃ አድርገህ ሹማቸው።
ጌታው ወደ ዳኞች ይውሰደው፤ ወደ በር ወይም ወደ በሩ መቃን ወስዶ ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ ከዚያም ዕድሜ ዘመኑን የርሱ አገልጋይ ይሆናል።
በአገር ውስጥ ድኻ ተጨቍኖ፣ ፍትሕ ተጓድሎ፣ መብትም ተረግጦ ብታይ፣ እንደነዚህ ባሉ ነገሮች አትደነቅ፤ ምክንያቱም አንዱን አለቃ የበላዩ ይመለከተዋል፤ በእነዚህ በሁለቱም ላይ ሌሎች ከፍ ያሉ አሉ።