La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 79:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ያዕቆብን በልተውታልና፤ መኖሪያ ቦታውንም ባድማ አድርገዋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ያዕቆብን በልተውታልና፥ መኖርያውንም ባድማ አድርገዋልና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህንንም የምታደርገው እነርሱ ሕዝቦችህን ስለ ገደሉና ርስታቸውን ስለ አወደሙ ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የኀ​ያ​ላን አም​ላክ አቤቱ፥ መል​ሰን፥ ፊት​ህ​ንም አብራ፥ እኛም እን​ድ​ና​ለን።

Ver Capítulo



መዝሙር 79:7
9 Referencias Cruzadas  

ምድሪቱም የሰንበት ዕረፍት አገኘች፤ በኤርምያስ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ ሰባው ዓመት እስኪያበቃ ድረስ፣ ባድማ በነበረችበት ዘመን ሁሉ ዐረፈች።


ዕሪያ ከዱር ወጥቶ ያበለሻሻታል፤ በሜዳ የሚንጋጋ እንስሳ ሁሉ ይበላታል።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ከልክ በላይ አትቈጣን፤ ኀጢአታችንንም ለዘላለም አታስብ፤ እባክህ ተለመነን፤ ፊትህን ወደ እኛ መልስ፤ ሁላችንም የአንተ ሕዝብ ነንና።


ሶርያውያን ከምሥራቅ፣ ፍልስጥኤማውያን ከምዕራብ፤ አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫጭቋታል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።


ያገኛቸው ሁሉ ይውጣቸዋል፤ ጠላቶቻቸውም፣ ‘እኛ በደለኞች አይደለንም፤ እነርሱ የአባቶቻቸውን ተስፋ እግዚአብሔርን፣ እውነተኛ ማደሪያቸው የሆነውን እግዚአብሔርን በድለዋል’ አሉ።


ሰላም አለ በሚሉ አሕዛብ ላይ ግን በጣም ተቈጥቻለሁ፤ በመጠኑ ተቈጥቼ ሳለሁ፣ እነርሱ ግን ጥፋቱ እንዲብስ አደረጉ።’