መዝሙር 73:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም ወደ አምላክ መቅደስ እስክገባ፣ መጨረሻቸውንም እስካይ ድረስ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ እግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ፥ ፍጻሜአቸውንም እስካስተውል ድረስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ መቅደስህ እስክገባ ድረስ ምንም ማወቅ አልቻልኩም፤ ወደ መቅደስህ በገባሁ ጊዜ ግን በክፉዎች ላይ ምን እንደሚደርስባቸው ተረዳሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ የምድር ዳርቻዎችን ሁሉ ሠራህ፤ በጋንና ክረምትን አንተ አደረግህ። |
እግዚአብሔርን አንዲት ነገር እለምነዋለሁ፤ እርሷንም እሻለሁ፤ ይኸውም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ውበት አይ ዘንድ፣ በመቅደሱም ሆኜ አሰላስል ዘንድ ነው።
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናት በነቢያቱ ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ይወድዳሉ፤ ፍጻሜው ሲደርስ ግን ምን ታደርጉ ይሆን?”
“እግዚአብሔር ግን፣ ‘አንተ ሞኝ፤ ነፍስህን በዚህች ሌሊት ከአንተ ሊወስዱ ይፈልጓታል፤ እንግዲህ፣ ለራስህ ያከማቸኸው ለማን ይሆናል?’ አለው።