መዝሙር 71:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተወለድሁ ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፤ ከእናቴ ማሕፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ፤ አንተ የዘወትር ምስጋናዬ ነህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፥ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፥ ሁልጊዜም ዝማሬዬ ለአንተ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በአንተ ላይ እታመናለሁ፤ ከእናቴ ማሕፀን እንድወለድ ያደረግኸኝ አንተ ነህ፤ እኔም ዘወትር አመሰግንሃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ጠል በባዘቶ ላይ፥ በምድርም ላይ እንደሚንጠባጠብ ጠብታ ይወርዳል። |
እናንተ ደሴቶች ስሙኝ፤ እናንተ በሩቅ ያላችሁ ሕዝቦች ይህን አድምጡ፤ በእናቴ ማሕፀን ሳለሁ እግዚአብሔር ጠራኝ፤ ከመወለዴ በፊት በስም ጠራኝ።
በእግዚአብሔር ዐይን ፊት ከብሬአለሁ፤ አምላኬ ጕልበት ሆኖልኛል፤ ባሪያው እንድሆን ከማሕፀን የሠራኝ፣ ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ፣ እስራኤልን ወደ እርሱ እንድሰበስብ ያደረገኝ፣ እግዚአብሔር አሁንም እንዲህ ይላል፤