መዝሙር 7:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕዝቦች ጉባኤ ይክበብህ፤ አንተም ከላይ ሆነህ ግዛቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ በመዓትህ ተነሥ፥ በጠላቶቼ ላይ በቁጣ ተነሣባቸው፥ አቤቱ አምላኬ፥ ባዘዝኸው ትእዛዝ ንቃ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቦችን ሁሉ በዙሪያህ ሰብስብ፤ ከላይም ሆነህ ንገሥ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሕዛብም ጉባኤ ይከብብሃል፤ ስለዚህም ወደ አርያም ተመለስ። |
አንተ እግዚአብሔር አምላክ፣ የሰራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ ሆይ፤ ሕዝቦችን ሁሉ ለመቅጣት ተነሥ፤ በተንኰላቸው በደል የሚፈጽሙትንም ሁሉ አትማራቸው። ሴላ
ከፍ ከፍ ያለውና ልዕልና ያለው እርሱ፣ ስሙም ቅዱስ የሆነው፣ ለዘላለም የሚኖረው እንዲህ ይላል፤ “የተዋረዱትን መንፈሳቸውን ለማነሣሣት፣ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ለማነቃቃት፣ ከፍ ባለውና በቅዱሱ ስፍራ እኖራለሁ፤ የተሰበረ ልብ ካለውና በመንፈሱ ከተዋረደው ጋራ እሆናለሁ።
“ሰማይ ሆይ፤ በርሷ ላይ ሐሤት አድርግ! ቅዱሳን፣ ሐዋርያትና ነቢያትም ሐሤት አድርጉ! በእናንተ ላይ ባደረሰችው ነገር እግዚአብሔር ፈርዶባታልና።”