ክፋትን እያማጠ ያለ ሰው፣ ቅጥፈትን አርግዞ፣ ሐሰትን ይወልዳል።
የሞት መሣርያንም አሰናድቷል፥ ፍላጻዎቹንም የሚንበለበሉ አደረገ።
ኃጢአተኞች በደልን ይፀንሳሉ፤ ተንኰልን ያረግዛሉ፤ ውሸትን ይወልዳሉ።
እነሆ፥ ዐመፀኛ በዐመፁ ተጨነቀ፤ ጭንቅን ፀነሰ፤ ኀጢአትንም ወለደ።
ክፉ ሰው ዕድሜውን ሙሉ፣ ጨካኙም በተመደበለት ዘመን ሁሉ ይሠቃያል።
መከራን ይፀንሳሉ፤ ክፋትንም ይወልዳሉ፤ በሆዳቸውም ተንኰል ይጠነስሳሉ።”
ገለባን ፀነሳችሁ፤ እብቅንም ወለዳችሁ፤ እስትንፋሳችሁም የሚበላችሁ እሳት ነው።
“በመዓት ላይ መዓት አመጣባቸዋለሁ። ፍላጻዬንም በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ።
ምኞትም ከፀነሰች በኋላ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።