ጐርፍ አያጥለቅልቀኝ፤ ጥልቅ ውሃም አይዋጠኝ፤ ጕድጓዱም ተደርምሶ አይዘጋብኝ።
እንዳይውጠኝ ከረግረግ አውጣኝ፥ ከሚጠሉኝና ከጥልቅ ውኃ አስጥለኝ።
ጐርፍ እንዳይወስደኝ፥ ጥልቅ ባሕር እንዳያሰጥመኝ፥ መቃብር እንዳይውጠኝ ጠብቀኝ።
ውሃው በምድር ላይ በጣም እየጨመረና ከፍ እያለ ሲሄድ፣ መርከቧ በውሃው ላይ ተንሳፈፈች።
በሲኦል አትተወኝምና፤ በአንተ የታመነውም መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም።
ዮናስ በትልቅ ዓሣ ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ቈየ፣ እንዲሁ የሰው ልጅም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በምድር ሆድ ውስጥ ይቈያል።
እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አስወግዶ አስነሣው፤ ሞት ይዞ ሊያስቀረው አልቻለምና።
ይህን አስቀድሞ በማየቱ እርሱ በሲኦል እንዳልቀረና ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ ተናገረ።