የምድረ በዳው ሣር እጅግ ለመለመ፤ ኰረብቶችም ደስታን ተጐናጸፉ።
በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ፈለጎችህ ስብን ይጠግባሉ።
የግጦሽ ስፍራዎች በመንጋ የተሞሉ ይሆናሉ፤ ተራራዎችም ደስታን እንደ ልብስ ይለብሳሉ።
በራሳችን ላይ ሰውን አስጫንህ፤ በእሳትና በውኃ መካከል አሳለፍኸን፥ ወደ ዕረፍትም አወጣኸን።
ተራሮችን በብርታትህ መሠረትህ፤ ኀይልንም ታጥቀሃል።
የዱር እንስሳት ሆይ፤ አትፍሩ፤ መሰማሪያ መስኮቹ ለምልመዋልና፤ ዛፎቹ ፍሬአቸውን አፍርተዋል፤ የበለሱ ዛፍና የወይኑ ተክልም እጅግ አፍርተዋል።