መዝሙር 63:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምሕረትህ ከሕይወት ይበልጣልና፤ ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ከሕይወት እንኳ የሚሻል ስለ ሆነ አመሰግንሃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ እባብ ምላሳቸውን አሰሉ፤ መራራ ነገርን ለማድረግ፥ |
የምትሉትን ቃል ይዛችሁ፣ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ እንዲህም በሉት፤ “ኀጢአታችንን ሁሉ ይቅር በለን፤ የከንፈራችንንም ፍሬ እንድናቀርብ፣ በምሕረትህ ተቀበለን።
እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኳችሁ ነው።
በተፈጥሮ ደካሞች ስለ ሆናችሁ፣ በሰው ቋንቋ ይህን እላለሁ፤ ብልቶቻችሁን በባርነት ለርኩሰትና እየባሰ ለሚሄድ ክፋት ታቀርቡ እንደ ነበር፣ አሁን ደግሞ ወደ ቅድስና ለሚወስደው ጽድቅ ባሪያ አድርጋችሁ አቅርቡ።
ወዳጆች ሆይ፤ እኛ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ወደ ፊት ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። እርሱ በሚገለጥበት ጊዜ እናየዋለን፤ እርሱን እንደምንመስልም እናውቃለን።