መዝሙር 57:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእኔ ያሰበውን ወደሚፈጽምልኝ አምላክ፣ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጮኻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማረኝ፥ አቤቱ፥ ማረኝ፥ ነፍሴ አንተን ታምናለችና፥ ጉዳት እስኪያልፍ ድረስ በክንፎችህ ጥላ እታመናለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚያስፈልገኝን ሁሉ ወደሚሰጠኝ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጣራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በልባችሁ በምድር ላይ ኀጢአትን ትሠራላችሁና፥ እጆቻችሁም ሽንገላን ይታታሉና። |
ከፍ ከፍ ያለውና ልዕልና ያለው እርሱ፣ ስሙም ቅዱስ የሆነው፣ ለዘላለም የሚኖረው እንዲህ ይላል፤ “የተዋረዱትን መንፈሳቸውን ለማነሣሣት፣ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ለማነቃቃት፣ ከፍ ባለውና በቅዱሱ ስፍራ እኖራለሁ፤ የተሰበረ ልብ ካለውና በመንፈሱ ከተዋረደው ጋራ እሆናለሁ።
ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ፤ ሁልጊዜም ታዛዦች እንደ ነበራችሁ ሁሉ፣ አሁንም እኔ በአጠገባችሁ ሳለሁ ብቻ ሳይሆን፣ ይልቁንም አሁን በሌለሁበት ጊዜ በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤
ፈቃዱን እንድታደርጉ በመልካም ነገር ሁሉ ያስታጥቃችሁ፤ ደስ የሚያሠኘውንም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእኛ ያድርግ፤ ለርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን። አሜን።