በአምላክ ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለሁ፥ በጌታ ቃሉን እወድሳለሁ።
በእርሱም ስለምታመን አልፈራም፤ ሰውስ ከቶ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
እግዚአብሔር በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ አለ፥ ክብሩም በምድር ሁሉ ላይ ነው።
እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኅኔ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር ለሕይወቴ ዐምባዋ ነው፤ ማንን እፈራለሁ?