መዝሙር 45:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ በውበትሽ ተማርኳል፤ ጌታሽ ነውና አክብሪው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፥ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በውበትሽ ንጉሡ ይወድሻል፤ ሆኖም ጌታሽ በመሆኑ እጅ በመንሣት አክብሪው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው። |
አንቺ ከሴቶች ሁሉ ይበልጥ የተዋብሽ ሆይ፤ የማታውቂ ከሆነ፣ የበጎቹን ዱካ ተከተዪ፤ የፍየል ግልገሎችሽንም፣ በእረኞቹ ድንኳን አጠገብ አሰማሪ።
አንቺ በገደል ዐለት ንቃቃት፣ በተራሮችም ባሉ መደበቂያ ስፍራዎች ውስጥ ያለሽ ርግቤ ሆይ! ፊትሽን አሳዪኝ፤ ድምፅሽንም አሰሚኝ፤ ድምፅሽ ጣፋጭ፣ መልክሽም ውብ ነውና።
እግዚአብሔር አምላክሽ በመካከልሽ አለ፤ እርሱ ብርቱ ታዳጊ ነው፤ በአንቺ እጅግ ደስ ይለዋል፤ በፍቅሩ ያሳርፍሻል፤ በዝማሬም በአንቺ ላይ ከብሮ ደስ ይሰኛል።”
ከዚህም በላይ ለርሱ ብዬ ሁሉን ነገር የተውሁለትን፣ ወደር የሌለውን ጌታዬን ክርስቶስ ኢየሱስን ከማወቅ ታላቅነት ጋራ ሳነጻጽር፣ ሁሉንም ነገር እንደ ጕድለት እቈጥረዋለሁ፤ ለርሱ ስል ሁሉን ዐጥቻለሁ፤ ክርስቶስን አገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤