እኔም፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረት አድርግልኝ፤ አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት” አልሁ።
ጌታ በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፥ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል።
እኔም “እግዚአብሔር ሆይ! አንተን ስለ በደልኩ ምሕረትን አድርግልኝ፤ ከሕመም ፈውሰኝ” አልኩ።
ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፤ በዓልን የሚያደርጉ ሰዎች በምስጋናና በደስታ ቃል ሲያመሰግኑ ተሰሙ።
ኀጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፣ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፣
ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል፤ ቍስላቸውንም ይጠግናል።
ኀጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፤ በደሌንም አልሸሸግሁም፤ ደግሞም “መተላለፌን ለእግዚአብሔር እናዘዛለሁ” አልሁ፤ አንተም የኀጢአቴን በደል፣ ይቅር አልህ። ሴላ
“ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰባብሮናል፤ እርሱም ይጠግነናል፤ እርሱ አቍስሎናል፤ እርሱም ይፈውሰናል።