እርሱም ወንድሞቹን፣ “ኧረ ብሬ ተመልሶልኛል፤ ይኸው ስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት” አላቸው። ሁሉም ልባቸው በድንጋጤ ተሞልቶ እየተንቀጠቀጡ በመተያየት፣ “እግዚአብሔር ምን ሊያመጣብን ይሆን?” አሉ።
መዝሙር 40:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስፍር ቍጥር የሌለው ክፋት ከብቦኛልና፤ የኀጢአቴ ብዛት ስለ ያዘኝ ማየት ተስኖኛል፤ ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዝቷል፤ ልቤም ከድቶኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ አንተ ርኅራኄህን ከእኔ አታርቅ፥ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከቊጥር በላይ የሆኑ ችግሮች ያስጨንቁኛል! በደሎቼ ስለ በዙ ማየት አልችልም፤ እነርሱም በቊጥር ከራስ ጠጒሮቼ ይበልጣሉ፤ ስለዚህ ልቤም እየከዳኝ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔን ግን ስለ የዋህነቴ ተቀበልኸኝ፥ በፊትህም ለዘለዓለም አጸናኸኝ። |
እርሱም ወንድሞቹን፣ “ኧረ ብሬ ተመልሶልኛል፤ ይኸው ስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት” አላቸው። ሁሉም ልባቸው በድንጋጤ ተሞልቶ እየተንቀጠቀጡ በመተያየት፣ “እግዚአብሔር ምን ሊያመጣብን ይሆን?” አሉ።
ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ፣ ከራሴ ጠጕር በዙ፤ ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልጉ፣ በከንቱም የሚጠሉኝ ብዙዎች ሆኑ፤ ያልሰረቅሁትን ነገር፣ መልሰህ አምጣ ተባልሁ።
በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት የለንምና፤ ነገር ግን እንደ እኛ በማንኛውም ነገር የተፈተነ ሊቀ ካህናት አለን፤ ይሁን እንጂ ምንም ኀጢአት አልሠራም።
እንዲሁም ክርስቶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኀጢአት ሞቷልና፤ ወደ እግዚአብሔር ያቀርባችሁ ዘንድ ጻድቅ የሆነው እርሱ ስለ ዐመፀኞች ሞተ፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤