ከጕዳትም ሁሉ የታደገኝ መልአክ፣ እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤ እነርሱም በስሜ፣ በአባቶቼ በአብርሃምና በይሥሐቅ ስም ይጠሩ፤ በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።”
መዝሙር 31:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንፈሴን በእጅህ እሰጣለሁ፤ እግዚአብሔር የእውነት አምላክ ሆይ፤ አንተ ተቤዠኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ መታመኛዬ ነህና ከደበቁብኝ ወጥመድ አውጣኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእውነት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ነፍሴን ለአንተ እሰጣለሁና አድነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአቴን ነገርሁ፤ በደሌንም አልሸሸግሁም፤ ስለ ኀጢአቴ ወደ እግዚአብሔር ራሴን እከስሳለሁ አልሁ፤ አንተም የልቤን ሽንገላ ተውልኝ። |
ከጕዳትም ሁሉ የታደገኝ መልአክ፣ እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤ እነርሱም በስሜ፣ በአባቶቼ በአብርሃምና በይሥሐቅ ስም ይጠሩ፤ በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።”
በመጣሁ ጊዜ ለምን በዚያ ሰው አልነበረም? በተጣራሁስ ጊዜ የሚመልስ ሰው እንዴት በዚያ ታጣ? ስለ እናንተ ወጆ ለመክፈል ክንዴ ዐጥራ ነበርን? እናንተንስ ለማዳን ኀይል አነሰኝን? እነሆ፤ በተግሣጼ ባሕሩን አደርቃለሁ፤ ወንዞችን ምድረ በዳ አደርጋለሁ፤ ዓሦቻቸው ውሃ በማጣት ይሸታሉ፤ በጥማትም ይሞታሉ።
መከራን የምቀበለውም ለዚሁ ነው፤ ሆኖም ያመንሁትን እርሱን ስለማውቅ አላፍርበትም፤ የሰጠሁትንም ዐደራ እስከዚያች ቀን ድረስ መጠበቅ እንደሚችል ተረድቻለሁ።
እግዚአብሔር ከቶ ሊዋሽ አይችልም፤ እርሱ በሁለት በማይለወጡ ነገሮች በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ወደ እርሱ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንድናገኝ አድርጓል።
እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ “መጽሐፉን ልትወስድ፣ ማኅተሞቹንም ልትፈታ ይገባሃል፤ ምክንያቱም ታርደሃል፤ በደምህም ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋ ሁሉ፣ ከወገን ሁሉ፣ ከሕዝብ ሁሉ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ዋጅተሃል።