መዝሙር 22:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጕልበቴ እንደ ገል ደረቀ፤ ምላሴ ከላንቃዬ ጋራ ተጣበቀ፤ ወደ ሞት ዐፈርም አወረድኸኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ውኃ ፈሰስሁ፥ አጥንቶቼም ሁሉ ተለያዩ፥ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፥ በአንጀቴም መካከል ቀለጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጒሮሮዬ እንደ ሸክላ ደረቀ፤ ምላሴም ከላንቃዬ ጋር ተጣበቀ፤ እንደ ሞተ ሰው በትቢያ ላይ ተውከኝ። |
በመሬት ላይ የፈሰሰ ውሃ እንደማይታፈስ ሁሉ፣ እኛም እንደዚሁ እንሞታለን፤ እግዚአብሔር ግን ከአገር የተሰደደ ሰው ከርሱ እንደ ራቀ በዚያው እንዳይቀር የሚመለስበትን ሁኔታ ያመቻቻል እንጂ ሕይወቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም።
መተላለፌን ለምን ይቅር አትልም? ኀጢአቴንስ ለምን አታስወግድልኝም? ትቢያ ውስጥ የምጋደምበት ጊዜ ደርሷል፤ ትፈልገኛለህ፤ እኔ ግን የለሁም።”
ስለዚህ ድርሻውን ከታላላቆች ጋራ እሰጠዋለሁ፤ ምርኮውን ከኀያላን ጋራ ይካፈላል፤ እስከ ሞት ድረስ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠቱ፣ ከክፉ አድራጊዎችም ጋራ በመቈጠሩ፣ የብዙዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤ ስለ ዐመፀኞችም ማለደ።