ከኢዮአካዝ ሰራዊት የተረፈው ዐምሳ ፈረሰኞች፣ ዐሥር ሠረገሎችና ዐሥር ሺሕ እግረኛ ወታደር ብቻ ነው፤ ይህ የሆነበትም ምክንያት የሶርያ ንጉሥ የቀረውን ስለ አጠፋውና እንደ ዐውድማ ብናኝ ስለ አደረገው ነበር።
መዝሙር 18:42 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ አደቀቅኋቸው፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም ረገጥኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጮኹ የሚረዳቸውም አልነበረም፥ ወደ ጌታ ጮኹ፥ ነገር ግን አልመለሰላችውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ እስኪሆኑ ድረስ አደቃቸዋለሁ፤ በመንገድ ላይ እንዳለ ጭቃም እረግጣቸዋለሁ። |
ከኢዮአካዝ ሰራዊት የተረፈው ዐምሳ ፈረሰኞች፣ ዐሥር ሠረገሎችና ዐሥር ሺሕ እግረኛ ወታደር ብቻ ነው፤ ይህ የሆነበትም ምክንያት የሶርያ ንጉሥ የቀረውን ስለ አጠፋውና እንደ ዐውድማ ብናኝ ስለ አደረገው ነበር።
ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፣ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፣ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፣ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፣ በሚያስቈጣኝም ሕዝብ ላይ እሰድደዋለሁ።
“ከምሥራቅ አንዱን ያነሣው፣ በጽድቅም ወደ አገልግሎቱ የጠራው ማን ነው? አሕዛብን አሳልፎ ሰጠው፤ ነገሥታትን በፊቱ አስገዛለት በሰይፉም እንደ ትቢያ አቦነናቸው፤ በቀስቱም በነፋስ እንደ ተበተነ ገለባ አደረጋቸው።
ጠላትን መንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ ይረጋግጣሉ፤ በአንድነት እንደ ጦር ሰልፈኛ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋራ ስለ ሆነ ተዋግተው፤ ፈረሰኞችን ያዋርዳሉ።