በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤ በነፋስም ክንፍ መጠቀ።
ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም፥ ጨለማ ከእግሩ በታች ነበረ።
በኪሩቤል ላይ ሆኖ በረረ፤ በነፋስ ክንፎች ላይ ሆኖ ወደ ላይ መጠቀ።
ከወርቅና ከክቡር ዕንቍ ይልቅ ይወደዳል፤ ከማርና ከማር ወለላም ይልቅ ይጣፍጣል።
የእልፍኝህን አግዳሚ በውሆች ላይ አኖርህ፤ ደመናትን ሠረገላህ አደረግህ፤ በነፋስ ክንፍ ትሄዳለህ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያትህን ሰንጥቀህ ውረድ፤ ይጤሱም ዘንድ ተራሮችን ዳስስ።
ዮሴፍን እንደ በግ መንጋ የምትመራ፣ የእስራኤል እረኛ ሆይ፤ ስማን፤ በኪሩቤል ላይ በዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፤ በብርሃንህ ተገለጥ።
እግዚአብሔር ነገሠ፤ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ፤ በኪሩቤል ላይ በዙፋን ተቀምጧል፤ ምድር ትናወጥ።
እኛ እኮ ጥንትም የአንተው ነን፤ እነርሱን ግን አንተ አላገዝሃቸውም፤ በስምህም አልተጠሩም።