መዝሙር 122:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም የፍርድ ዙፋኖች የሆኑት፣ የዳዊት ቤት ዙፋኖች ተዘርግተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዙፋኖች በዚያ ለፍርድ ተቀምጠዋልና፥ የዳዊት ቤት ዙፋኖች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዳዊት ዘር የነገሡ ሁሉ ሕዝባቸውን ለመዳኘት በዚህች ከተማ ይቀመጡ ነበር። |
ዳኝነት የሚያይበትንም የዙፋን ችሎት አዳራሽ ሠራ፤ ይኸውም የፍትሕ አዳራሽ የተባለው ነው፤ ይህንም ከወለሉ አንሥቶ እስከ ጣራው ድረስ በዝግባ ሳንቃ ሸፈነው።
ኢዮሣፍጥም በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ሕግ እንዲያስፈጽሙና ለሚነሡ ክርክሮችም እልባት እንዲሰጡ ከሌዋውያን፣ ከካህናትና ከእስራኤል ቤት አለቆች ጥቂት ሰዎች ሾመ፤ እነርሱም መኖሪያቸው በኢየሩሳሌም ሆነ።
በአንድ የነፍስ ግድያ ዐይነትና በሌላ፣ በአንድ ዐይነት ሕጋዊ ክርክርና በሌላ፣ ወይም በአንድ የክስ ዐይነትና በሌላ መካከል ውሳኔ የሚጠይቅ ማንኛውም ጕዳይ ቢነሣ፣ ከዐቅምህ በላይ የሆነ ጕዳይ በከተሞችህ ውስጥ ቢያጋጥምህ፣ ተነሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ስፍራ ውጣ፤