በሰዎች ዘንድ ክፋት ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ፣ ዐመፀኞች በየአቅጣጫው በዛቻ ይዞራሉ።
አቤቱ፥ አንተ ጠብቀን፥ ከዚህችም ትውልድ ለዘለዓለም ታደገን።
ክፉ ነገር በሰዎች ዘንድ በሚመሰገንበት ጊዜ ክፉ ሰዎች በኩራት ይመላለሱበታል።
ስማቸው የማይታወቅ ሞኞች ናቸው፤ ከምድሪቱም ተባርረዋል።
ገዥ የሐሰት ወሬ የሚሰማ ከሆነ፣ ሹማምቱ ሁሉ ክፉዎች ይሆናሉ።
“በርሱም ፈንታ የተናቀ ሰው ይነግሣል፤ ንጉሣዊ ክብርም አይሰጠውም፤ ሕዝቡ በሰላም ተቀምጦ ሳለ በተንኰል መንግሥቱን ይይዛል።
ጣዖትን መከተል በመውደዱ፣ ኤፍሬም ተጨቍኗል፤ በፍርድም ተረግጧል።
የዖምሪን ሥርዐት፣ የአክዓብን ቤት ልምድ ሁሉ የሙጥኝ ብለሃል፤ ትውፊታቸውንም ተከትለሃል። ስለዚህ አንተን ለውድመት፣ ሕዝብህን ለመዘባበቻ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ አሕዛብም ይሣለቁብሃል።”