መዝሙር 115:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል ቤት ሆይ፤ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በጌታ ታመኑ፥ ረድኤታቸውና መከታቸው እርሱ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ግን የሚረዳችሁና የሚጠብቃችሁ እግዚአብሔር ስለ ሆነ በእርሱ ታመኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ፥ |
እግዚአብሔር አምላክ ፀሓይና ጋሻ ነውና፤ እግዚአብሔር ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ያለ ነቀፋ የሚሄዱትን፣ መልካም ነገር አይነፍጋቸውም።
አሁንም በፍጹም ብትታዘዙኝና ቃል ኪዳኔን ብትጠብቁ እነሆ ከአሕዛብ ሁሉ እናንተ የተወደደ ርስቴ ትሆናላችሁ፤ ምንም እንኳ ምድር ሁሉ የእኔ ብትሆንም፣
ብፁዕ ነህ፤ አንተ እስራኤል ሆይ፤ እግዚአብሔር ያዳነው ሕዝብ፣ እንደ አንተ ያለ ማን አለ? እርሱ ጋሻህና ረዳትህ፣ የክብርህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህ በፍርሀት ከፊትህ ያፈገፍጋሉ፤ አንተም የማምለኪያ ኰረብታቸውን መረማመጃ ታደርጋለህ።”