እንግዲህ በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የአውራጃዪቱ መሪዎች እነዚህ ናቸው፤ በዚህ ጊዜም በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩ የተወሰኑ እስራኤላውያን፣ ካህናት፣ ሌዋውያን፣ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች እያንዳንዳቸው በተለያዩ ከተሞች ባለ በየራሳቸው ንብረት ላይ ተቀመጡ፤
መዝሙር 107:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደሚኖሩባትም ከተማ፣ በቀና መንገድ መራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደሚኖሩበት ከተማ ይሄዱ ዘንድ በቀና መንገድን መራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ሊኖሩ ወደሚችሉበት ከተማ በትክክለኛ መንገድ መራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በመቅደሱ ተናገረ፥ ደስ ይለኛል፥ ሰቂማንም እካፈላለሁ፥ የሸለቆ ቦታዎችን እሰፍራለሁ። |
እንግዲህ በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የአውራጃዪቱ መሪዎች እነዚህ ናቸው፤ በዚህ ጊዜም በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩ የተወሰኑ እስራኤላውያን፣ ካህናት፣ ሌዋውያን፣ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች እያንዳንዳቸው በተለያዩ ከተሞች ባለ በየራሳቸው ንብረት ላይ ተቀመጡ፤
የተቤዠህ፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የሚበጅህ ምን እንደ ሆነ የማስተምርህ፣ መሄድ በሚገባህ መንገድ የምመራህ ነኝ።
እያለቀሱ ይመጣሉ፤ እያጽናናሁ አመጣቸዋለሁ፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፣ ኤፍሬም በኵር ልጄ ነውና፣ በውሃ ምንጭ ዳር፣ በማይሰናከሉበት ቀና መንገድ እመራቸዋለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “መንታ መንገድ ላይ ቁሙ፣ ተመልከቱም፤ መልካሟን፣ የጥንቷን መንገድ ጠይቁ፤ በርሷም ላይ ሂዱ። ለነፍሳችሁ ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እናንተ ግን፣ ‘በርሷ አንሄድም’ አላችሁ።
እናንተ ግን ወደ ጽዮን ተራራ፣ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም፣ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ መጥታችኋል፤ በደስታ ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፣