መዝሙር 102:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትነሣለህ፤ ጽዮንንም በርኅራኄ ዐይን ታያለህ፤ ለርሷ በጎነትህን የምታሳይበት ዘመን ነውና፤ የተወሰነውም ጊዜ ደርሷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ለዘለዓለም ትኖራለህ፥ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለጽዮን ምሕረት የምታደርግላት ጊዜ ስለ ተቃረበና ጊዜውም አሁን ስለ ሆነ አንተ ትነሣለህ፤ ለእርስዋም ትራራለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራላቸዋል፤ |
ደግሞም እግዚአብሔርም ሙሴን፣ “ ‘የአባቶቻችሁ የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ የሆነው እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛል፤’ “ስሜም ለዘለዓለም ይኸው ነው፤ ወደ ፊት በተከታታይ በሚነሣው ትውልድ ሁሉ የምታሰበው በዚህ ስም ነው ብለህ ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው” አለው።
ከዚያ ሕዝብ ለሚመጡ መልእክተኞች ምን መልስ ይሰጣል? “መልሱ፣ ‘እግዚአብሔር ጽዮንን መሥርቷል፤ መከራን የተቀበለው ሕዝብም፣ በርሷ ውስጥ መጠጊያን አግኝቷል’ የሚል ነው።”
ለኢየሩሳሌም አለዝባችሁ ንገሯት፤ ዐውጁላትም፤ በባርነት ያገለገለችበት ዘመን አብቅቷል፤ የኀጢአቷም ዋጋ ተከፍሏል፤ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ከእግዚአብሔር እጅ ሁለት ዕጥፍ ተቀብላለች።
የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ምርኳቸውን በመለስሁላቸው ጊዜ፣ እነርሱ በይሁዳ ምድርና በከተሞቿ፣ ‘አንተ የጽድቅ ማደሪያ ቅዱስ ተራራ ሆይ፤ እግዚአብሔር ይባርክህ!’ የሚል አነጋገር እንደ ገና ይጠቀማሉ።
ደግሞም የእግዚአብሔርን ቀን እየተጠባበቃችሁ መምጫውን ልታፋጥኑ ይገባል። በዚያ ቀን ሰማያት በእሳት ተቃጥለው ይጠፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በታላቅ ትኵሳት ይቀልጣል።