መዝሙር 10:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ሰው ከትዕቢቱ የተነሣ እግዚአብሔርን አይፈልግም፤ በሐሳቡም ሁሉ አምላክ የለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ በትዕቢቱ ጌታን አይፈልገውም፥ በሐሳቡ በሙሉ እግዚአብሔር የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉዎች ስለ እግዚአብሔር ግድ የላቸውም በትዕቢታቸውም እግዚአብሔር የለም ብለው ያስባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በቤተ መቅደሱ ነው፤ እግዚአብሔር ዙፋኑ በሰማይ ነው፤ ዐይኖቹም ወደ ድሃ ይመለከታሉ፤ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ። |
አለዚያ ግን ያለ ልክ እጠግብና እክድሃለሁ፤ ‘እግዚአብሔር ማን ነው?’ እላለሁ፤ ወይም ድኻ እሆንና እሰርቃለሁ፤ የአምላኬንም ስም አሰድባለሁ።
ለዐመፀኛ ሕዝብ፣ መልካም ባልሆኑ መንገዶች ለሚሄዱ፣ የልባቸውን ምኞት ለሚከተሉ፣ ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ። ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝቦች፣
“የዚህ ትውልድ ሰዎች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አስተውሉ፤ “እኔ ለእስራኤል ሕዝብ ምድረ በዳ፣ ወይስ ድቅድቅ ጨለማ ያለበት ምድር ሆንሁበትን? ሕዝቤ፣ ‘እንደ ልባችን ልንሆን እንፈልጋለን፤ ተመልሰንም ወደ አንተ አንመጣም’ ለምን ይላል?
በዚያ ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ ተንደላቅቀው የሚኖሩትን፣ በዝቃጩ ላይ እንደ ቀረ የወይን ጠጅ የሆኑትን፣ ‘ክፉም ይሁን መልካም፣ እግዚአብሔር ምንም አያደርግም’ የሚሉትን ቸልተኞች እቀጣለሁ።
እናንተ የምድር ትሑታን ሁሉ፣ ትእዛዙን የምትፈጽሙ፣ እግዚአብሔርን እሹ፤ ጽድቅንና ትሕትናን ፈልጉ፤ በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን፣ ትሰወሩ ይሆናል።
እግዚአብሔርን ቢያውቁም እንኳ፣ እንደ አምላክነቱ አላከበሩትም፤ ምስጋናም አላቀረቡለትም፤ ነገር ግን ሐሳባቸው ፍሬ ቢስ ሆነ፤ የማያስተውል ልባቸው ጨለመ።
ከዚህም በላይ በሐሳባቸው እግዚአብሔርን ማወቅ አይጠቅምም በማለታቸው፣ መደረግ የማይገባውን እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው።
በዚያ ዘመን ከክርስቶስ ተለይታችሁ፣ ከእስራኤል ወገንነት ርቃችሁ፣ ለኪዳኑም ተስፋ ባዕዳን ሆናችሁ፣ በዓለም ላይ ያለ ተስፋና ያለ እግዚአብሔር እንደ ነበራችሁ አስታውሱ።