መዝሙር 10:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በልቡም፣ “እግዚአብሔር ረስቷል፤ ፊቱን ሸፍኗል፤ ፈጽሞም አያይም” ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልቡም እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔር ረስቶኛል፥ ፈጽሞም እንዳያይ ፊቱን ሰወረ”። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአተኛ በሐሳቡ፦ “እግዚአብሔር ረስቶአል፤ ፊቱንም ሸፍኖ በፍጹም አያይም!” ይላል። |
እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዳቸው በጣዖታቸው ምስል ጓዳ ውስጥ በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱ፣ ‘እግዚአብሔር አያየንም፤ እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቷል ይላሉ’ ” አለኝ።
እርሱም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፤ “የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ኀጢአት እጅግ በዝቷል፤ ምድሪቱ በደም ተጥለቅልቃለች፤ ከተማዪቱም ግፍን ተሞልታለች። እነርሱ፣ ‘እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቷታል፤ እግዚአብሔር አያይም’ ይላሉ፤
የጋበዘውም ፈሪሳዊ ይህን ባየ ጊዜ፣ “ይህ ሰው ነቢይ ቢሆን ኖሮ፣ የነካችው ሴት ማን እንደ ሆነች፣ ደግሞም ምን ዐይነት ሰው እንደ ሆነች ባወቀ ነበር፤ ኀጢአተኛ ናትና” ብሎ በልቡ ዐሰበ።