ምሳሌ 8:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአንደበቴ የሚወጡት ቃሎች ሁሉ ጽድቅ ናቸው፤ አንዳቸውም ጠማማና ግራ የሚያጋቡ አይደሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአፌ ቃላት ሁሉ ጽድቅ ናቸው፥ በውስጣቸውም ምንም ጠማማና ጠመዝማዛ ነገር የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የምናገረው ሁሉ እውነት ነው፤ ጠማማ ወይም ወልጋዳ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአፌ ቃላት ሁሉ እውነት ናቸው፤ ጠማማና እንቅፋት በውስጣቸው የለም። |
ይህ ከኤዶም፣ ቀይ የተነከረ መጐናጸፊያ ለብሶ ከባሶራ የሚመጣ ማን ነው? ይህ ክብርን የተጐናጸፈ፣ በኀይሉ ታላቅነት እየተራመደ የሚመጣውስ ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር፣ ለማዳንም ኀይል ያለኝ እኔው ነኝ።”
ይኸውም በጠማማና በክፉ ትውልድ መካከል ንጹሓንና ያለ ነቀፋ፣ ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች ሆናችሁ፣ እንደ ከዋክብት በዓለም ሁሉ ታበሩ ዘንድ ነው።