ምሳሌ 8:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ከተማዪቱ በሚያስገቡት በሮች አጠገብ፣ በመግቢያዎቹ ላይ፣ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ እንዲህ ስትል ትጮኻለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በበሮች አጠገብ በከተማይቱም መግቢያ፥ በደጆች መግቢያ ትጮኻለች፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከተማው መግቢያ በሮች ላይ ሆና እንዲህ ስትል ትጮኻለች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኀያላን በሮች ትጠብቃለች፥ በመግቢያዉም ትመሰገናለች፥ |
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እኔ ለዓለም በግልጽ ተናግሬአለሁ፤ አይሁድ በተሰበሰቡበት ምኵራብ፣ በቤተ መቅደስም ሁልጊዜ አስተምሬአለሁ፤ በስውር የተናገርሁት የለም።