“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፤ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ስለሚመረምርና ሐሳብን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ የአባትህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በበጎ ፈቃድ አገልግለው። ከፈለግኸው ታገኘዋለህ፤ ከተውኸው ግን እርሱም ለዘላለም ይተውሃል።
ምሳሌ 3:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤ እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔርን መሪ አድርገው፤ እርሱም በትክክለኛው መንገድ ይመራሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንገድህ ሁሉ ጥበብን ዕወቃት፥ እርስዋም መንገድህን ታቃናልሃለች። |
“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፤ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ስለሚመረምርና ሐሳብን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ የአባትህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በበጎ ፈቃድ አገልግለው። ከፈለግኸው ታገኘዋለህ፤ ከተውኸው ግን እርሱም ለዘላለም ይተውሃል።
ጌታ ሆይ፤ የባሪያህን ጸሎት፣ ስምህን በመፍራት ደስ የሚሰኙትን የባሪያዎችህንም ጸሎት ጆሮህ ታድምጥ። በዚህ ሰው ፊት ሞገስን አድርገህለት ዛሬ ለባሪያህ መከናወንን ስጠው።” በዚያ ጊዜ እኔ የንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርሁ።
ስለዚህ መኳንንቱን፣ ሹማምቱንና ተራውን ሕዝብ ሰብስቤ በየቤተ ሰቡ ይመዘገቡ ዘንድ እግዚአብሔር ይህን በልቤ አኖረ። ወደ ምድራቸው ለመመለስ የመጀመሪያ የሆኑትን ሰዎች የትውልድ ሐረግ መዝገብ አገኘሁ፤ ተጽፎ ያገኘሁትም ይህ ነው።
ቂሮስን በጽድቅ አስነሥቻለሁ፤ መንገዱን ሁሉ አስተካክዬለታለሁ፤ ከተማዬን እንደ ገና ይሠራታል፤ ምርኮኞቼን ያለ ክፍያ ወይም ያለ ዋጋ፣ ነጻ ያወጣል፤’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”
የተቤዠህ፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የሚበጅህ ምን እንደ ሆነ የማስተምርህ፣ መሄድ በሚገባህ መንገድ የምመራህ ነኝ።
አንዳንድ ጊዜ ደመናው በድንኳኑ ላይ የሚቈየው ለጥቂት ቀን ብቻ ነበር፤ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሰፍራሉ፤ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ጕዞ ይጀምራሉ፤
ዳዊትም፣ “ይህን ወራሪ ሰራዊት ልከተለውን? እደርስባቸዋለሁን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፣ “በርግጥ ትደርስባቸዋለህ፤ ምርኮውንም ትመልሳለህ፤ ተከተል” ሲል መለሰለት።