ምሳሌ 23:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የርሱ ጣፋጭ መብል አያስጐምጅህ፤ ምግቡ አታላይ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጣፋጩ መብል አይመርህ የሐሰት እንጀራ ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናልባት ሊታዘብህ ስለሚችል የሚያቀርብልህን መልካም ምግብ ተስገብግበህ አትብላ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብትሳሳ ግን ምግቡን አትውደድ እርሱ የሐሰት እንጀራ ነውና። |
ንጉሡም በየዕለቱ የሚበሉትን ምግብና የሚጠጡትን የወይን ጠጅ ከንጉሡ ማእድ ድርጎ እንዲሰጣቸው አደረገ፤ ለሦስት ዓመት ከሠለጠኑ በኋላ በንጉሡ አገልግሎት ላይ የሚሰማሩ ናቸው።
“እንግዲህ በገደብ የለሽ ሕይወት፣ በመጠጥ ብዛትና ስለ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝልና ያ ቀን እንደ ወጥመድ ድንገት እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፤