የነቢያት ማኅበር ወገን ከሆነው የአንደኛው ሚስት፣ “አገልጋይህ ባሌ ሞቷል፤ እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ነበር አንተ ታውቃለህ፤ አሁን ግን ባለዕዳ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ባሪያ አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቷል” ስትል ወደ ኤልሳዕ ጮኸች።
ምሳሌ 22:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባለጠጋ ድኻን ይገዛል፤ ተበዳሪም የአበዳሪ ባሪያ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀብታም ድሆችን ይገዛል፥ ተበዳሪም የአበዳሪ ጥገኛ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድኻ የሀብታም ሰው አገልጋይ ነው፤ ገንዘብ የሚበደር የአበዳሪው ባሪያ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድሆች ባለጠጎችን ይገዛሉ፥ አገልጋዮችም ለጌቶቻቸው ያበድራሉ። |
የነቢያት ማኅበር ወገን ከሆነው የአንደኛው ሚስት፣ “አገልጋይህ ባሌ ሞቷል፤ እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ነበር አንተ ታውቃለህ፤ አሁን ግን ባለዕዳ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ባሪያ አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቷል” ስትል ወደ ኤልሳዕ ጮኸች።
ነገሩ ሁሉ አንድ ዐይነት ይሆናል፤ በሕዝቡ ላይ የሚሆነው በካህኑ፣ በአገልጋዩ ላይ የሚሆነው በጌታው፣ በአገልጋይዋ ላይ የሚሆነው በእመቤቷ፣ በገዥው ላይ የሚሆነው በሻጩ፣ በተበዳሪው ላይ የሚሆነው በአበዳሪው፣ በብድር ከፋይ ላይ የሚሆነው በብድር ሰጪው ይሆናል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የእስራኤል ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ ጻድቁን ስለ ጥሬ ብር፣ ድኻውንም ስለ ጥንድ ጫማ ይሸጡታልና።
እናንተ በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ የባሳን ላሞች፤ ድኾችን የምትጨቍኑና ችግረኞችን የምታስጨንቁ፣ ባሎቻችሁንም፣ “መጠጥ አቅርቡልን” የምትሉ ሴቶች ይህን ቃል ስሙ፤
ልብ በሉ፤ ዕርሻችሁን ሲያጭዱ ለዋሉ ሠራተኞች ያልከፈላችሁት ደመወዝ በእናንተ ላይ ይጮኻል፤ የዐጫጆቹም ጩኸት ሁሉን ቻይ ወደ ሆነው ጌታ ጆሮ ደርሷል።