La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 20:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሥ ለፍርድ ዙፋኑ ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣ ክፉውን ሁሉ በዐይኖቹ አበጥሮ ይለያል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በፍርድ ወንበር የተቀመጠ ንጉሥ ክፉውን ሁሉ በዐይኖቹ ይበትናል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በፍርድ ዙፋን ላይ የተቀመጠ ንጉሥ ክፉ የሆነውን ነገር ሁሉ አበጥሮ የሚያውቅ ዐይን አለው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እውነተኛ ንጉሥ በዙፋኑ በተቀመጠ ጊዜ በዐይኖቹ ፊት ምንም ክፉ አይቃወመውም።

Ver Capítulo



ምሳሌ 20:8
13 Referencias Cruzadas  

እርሱ፣ ደመና በሌለበት፣ በማለዳ ፀሓይ በምትወጣበት ጊዜ፣ እንዳለው ብርሃን ነው፤ በምድር ላይ ሣርን እንደሚያበቅለው፣ ከዝናብም በኋላ እንዳለው የብርሃን ጸዳል ነው።’


ዳኝነት የሚያይበትንም የዙፋን ችሎት አዳራሽ ሠራ፤ ይኸውም የፍትሕ አዳራሽ የተባለው ነው፤ ይህንም ከወለሉ አንሥቶ እስከ ጣራው ድረስ በዝግባ ሳንቃ ሸፈነው።


ለተቸገረው ሕዝብ ይሟገታል፤ የድኾችን ልጆች ያድናል፤ ጨቋኙንም ያደቅቀዋል።


ጠላቶችህ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ይጠፋሉና፤ ክፉ አድራጊዎችም ሁሉ ይበተናሉ።


ፍትሕን የምትወድድ፣ ኀያል ንጉሥ ሆይ፤ አንተ ትክክለኝነትን መሠረትህ፤ ፍትሕንና ቅንነትንም፣ ለያዕቆብ አደረግህ።


ክፋትን ማድረግ ለነገሥታት አስጸያፊ ነው፤ ዙፋን የሚጸናው በጽድቅ ነውና።


ጠቢብ ንጉሥ ክፉዎችን አበጥሮ ይለያል፤ የመውቂያ መንኰራኵርንም በላያቸው ላይ ይነዳል።


ክፉን ከንጉሥ ፊት አርቅ፤ ዙፋኑም በጽድቅ ትጸናለች።


ንጉሥ ለድኻ ትክክለኛ ፍርድ ቢሰጥ፣ ዙፋኑ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል።


እነሆ፤ ንጉሥ በጽድቅ ይነግሣል፤ ገዦችም በፍትሕ ይገዛሉ።


“ከእኔ ጋራ ያልሆነ ይቃወመኛል፤ ከእኔም ጋራ የማይሰበስብ ይበትናል።