ምሳሌ 20:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙ ሰው ጽኑ ፍቅር እንዳለው ይናገራል፤ ታማኝን ሰው ግን ማን ሊያገኘው ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ ሰዎች ቸርነታቸውን ያወራሉ፥ የታመነውን ሰው ግን ማን ያገኘዋል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው ሁሉ ስለ ራሱ ደግነት ያወራል፤ ነገር ግን በእውነት ታማኝ የሆነውን ሰው ማን ሊያገኝ ይችላል! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይቅር ባይ ሰው ታላቅና ክቡር ነው፤ ነገር ግን የታመነ ሰው የሚገኘው በድካም ነው። |
ገና በመመርመር ላይ ሳለሁ፣ ግን ያላገኘሁት፣ ከሺሕ ወንዶች መካከል አንድ ቅን ሰው አገኘሁ፣ በእነዚያ ሁሉ መካከል ግን አንዲት ቅን ሴት አላገኘሁም።
“በኢየሩሳሌም መንገዶች እስኪ ውጡ፤ ወደ ላይ ወደ ታችም ውረዱ፤ ዙሪያውን ተመልከቱ ቃኙ፤ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ እውነትን የሚሻና በቅንነት የሚሄድ፣ አንድ ሰው እንኳ ብታገኙ፣ እኔ ይህችን ከተማ እምራታለሁ።
ለእኔ ወዮልኝ! የወይን ዕርሻ በሚቃረምበት ጊዜ፣ የበጋ ፍራፍሬ እንደሚለቅም ሰው ሆኛለሁ፤ የሚበላ የወይን ዘለላ የለም፤ የምንጓጓለት፣ ቶሎ የሚደርሰው በለስም አልተገኘም።
“ግብዞች በሰዎች ዘንድ ለመከበር ብለው በየጐዳናውና በየምኵራቡ እንደሚያደርጉት፣ አንተም ለድኾች ምጽዋት በምትሰጥበት ጊዜ ይታይልኝ ብለህ ጥሩንባ አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ እንዲህ የሚያደርጉ ዋጋቸውን በሙሉ ተቀብለዋል።
ፈሪሳዊውም ቆሞ ስለ ራሱ እንዲህ ይጸልይ ነበር፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ እንደ ሌላው ሰው ሁሉ ቀማኛ፣ ዐመፀኛ፣ አመንዝራ፣ ይልቁንም እንደዚህ ቀረጥ ሰብሳቢ ባለመሆኔ አመሰግንሃለሁ፤
በመመካቴ ሞኝ ሆኛለሁ፤ ለዚህም ያበቃችሁኝ እናንተ ናችሁ፤ ስለ እኔ መመስከር የሚገባችሁ እናንተ ነበራችሁ። ደግሞም እኔ ከምንም የማልቈጠር ብሆንም፣ “ታላላቅ ሐዋርያት” ከሚባሉት በምንም አላንስም።