ምሳሌ 2:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጆሮህን ወደ ጥበብ ብታቀና፣ ልብህንም ወደ ማስተዋል ብትመልስ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጆሮህ ጥበብን እንዲያደምጥ ታደርጋለህ፥ ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጥበብን ቃል አድምጥ፤ በጥንቃቄም አስተውለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጆሮህ ጥበብን ትሰማለች፥ ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ። ልብህንም ልጅህን ለመምከር ታቀርባለህ፥ |
ጆሯችሁን ከፍታችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ ነፍሳችሁም እንድትኖር አድምጡኝ። ለዳዊት በገባሁት በጽኑ ፍቅሬ፣ ከእናንተም ጋራ የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።
የቤርያ ሰዎች ከተሰሎንቄ ሰዎች ይልቅ አስተዋዮች ስለ ነበሩ፣ “ነገሩ እንደዚህ ይሆንን?” እያሉ መጻሕፍትን በየዕለቱ በመመርመር ቃሉን በታላቅ ጕጕት ተቀብለዋል።