ምሳሌ 18:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞኝ ሰው አፉ መጥፊያው ነው፤ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰነፍ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሩም ለነፍሱ ወጥመድ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞኝ በሚናገርበት ጊዜ ራሱን በጒዳት ላይ ይጥላል፤ አነጋገሩም ወጥመድ ሆኖ ይይዘዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአላዋቂ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው። |
ባያትም ጊዜ ልብሱን በመቅደድ፣ “ወይኔ ልጄ ጕድ አደረግሽኝ! ጭንቅም ላይ ጣልሽኝ፤ ማስቀረት የማልችለውን ስእለት ለእግዚአብሔር ተስያለሁና” ብሎ በሐዘን ጮኸ።