ምሳሌ 14:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሞኝ ሰው ራቅ፣ ከከንፈሮቹ ዕውቀት አታገኝምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰነፍ ሰው ፊት ራቅ፥ በእርሱ ዘንድ የእውቀትን ከንፈር አታገኝምና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱ የምትማረው ምንም ዕውቀት ስለሌለ ከሞኞች ራቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰነፍ ሰው ፊት ሁሉ ጠማማ ነው፥ የብልሆች ከንፈር ግን የዕውቀት ጋሻ ነው። |
ሐናንያም በሕዝቡም ፊት፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነፆርን ቀንበር ከሕዝቡ ሁሉ ጫንቃ ላይ ልክ እንደዚህ እሰብራለሁ’ ” አለ። በዚህ ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ ትቶት መንገዱን ቀጠለ።
ነገር ግን አሁን የጻፍሁላችሁ፣ “ወንድም ነኝ” እያለ ከሚሴስን ወይም ከሚስገበገብ ወይም ጣዖትን ከሚያመልክ ወይም ከሚሳደብ ወይም ከሚሰክር ወይም ከሚቀማ ጋራ እንዳትተባበሩ ነው፤ ከእንደዚህ ዐይነቱ ሰው ጋራ ምግብ እንኳ አትብሉ።