ከዚያም ሁለት ምናምንቴ ሰዎች መጥተው ከፊት ለፊቱ ተቀመጡ፤ በሕዝቡም ፊት፣ “ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቧል” ብለው መሰከሩበት። ስለዚህ ከከተማዪቱ ውጭ ወስደው በድንጋይ ወግረው ገደሉት።
ምሳሌ 14:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታማኝ ምስክር አይዋሽም፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይዘከዝካል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የታመነ ምስክር አይዋሽም፥ የሐሰት ምስክር ግን በሐሰት ይናገራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታማኝ ምስክር አይዋሽም፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን የሚናገረው ሐሰት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የታመነ ምስክር አይዋሽም፤ የሐሰት ምስክር ግን ሐሰትን ያቀጣጥላል። |
ከዚያም ሁለት ምናምንቴ ሰዎች መጥተው ከፊት ለፊቱ ተቀመጡ፤ በሕዝቡም ፊት፣ “ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቧል” ብለው መሰከሩበት። ስለዚህ ከከተማዪቱ ውጭ ወስደው በድንጋይ ወግረው ገደሉት።
እንዲሁም ታማኝ ምስክር፣ ከሙታን በኵርና የምድር ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደንና ከኀጢአታችንም በደሙ ነጻ ላወጣን፣
“በሎዶቅያ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ አሜን የሆነው፣ ደግሞም ታማኝና እውነተኛ ምስክር የሆነው፣ የእግዚአብሔርም ፍጥረት ምንጭ የሆነው እንዲህ ይላል።