ምሳሌ 13:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጽድቅ ቅን የሆነውን ሰው ትጠብቀዋለች፤ ክፋት ግን ኀጢአተኛውን ትጥለዋለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንገዱ ያለ ነውር የሚሄደውን ጽድቅ ይጠብቀዋል፥ ኃጢአት ግን ኃጢአተኛውን ይጥለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደጋግ ሰዎች ደግነታቸው ይጠብቃቸዋል፤ ኃጢአተኞችን ግን ኃጢአታቸው ያጠፋቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንገዳቸው ቀና የሆነውን የዋሃንን ጽድቅ ትጠብቃቸዋለች፤ ኀጢአተኞችን ግን ኀጢአታቸው በደለኛ ታደርጋቸዋለች። |
እርሱም “የሶርያ ነገሥታት አማልክት እነርሱን ስለ ረዷቸው፣ እኔንም ይረዱኝ ዘንድ እሠዋላቸዋለሁ” ሲል እርሱን ላሸነፉት የደማስቆ አማልክት መሥዋዕት አቀረበ። ነገር ግን ለርሱና ለመላው እስራኤል መሰናክል ሆኑ።