ምሳሌ 13:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስተዋይ ሰው ሥራውን በዕውቀት ያከናውናል፤ ሞኝ ግን ቂልነቱን ይገልጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብልህ ሁሉ በእውቀት ይሠራል፥ ሰነፍ ግን ስንፍናውን ይገልጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አስተዋይ ሰዎች ለሚሠሩት ሥራ አስቀድመው ዕቅድ ያወጣሉ፤ ማስተዋል የጐደላቸው ሰዎች ግን አላዋቂነታቸውን ይገልጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብልህ ሁሉ በዕውቀት ይሠራል፤ ሰነፍ ግን ክፋቱን ይገልጣል። |
የእናንተን ታዛዥነት ሁሉም ሰምተዋል፤ በዚህም እኔ እጅግ ተደስቻለሁ። ሆኖም በጎ ስለ ሆነው ነገር ጥበበኞች፣ ክፉ ስለ ሆነውም የዋሆች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ።
አሁንም በጌታችንና በመላው ቤተ ሰቡ ላይ መከራ እያንዣበበ ስለ ሆነ፣ አስቢበትና የምታደርጊውን አድርጊ፤ እርሱ እንደ ሆነ እንዲህ ያለ ምናምንቴ ሰው ስለ ሆነ፣ ደፍሮ የሚነግረው አንድም ሰው የለም።”
ጌታዬ፣ ያን ምናምንቴ ሰው ናባልን ከቁም ነገር አይቍጠረው፤ ስሙ ራሱ ሞኝ ማለት ስለ ሆነ፣ ሰውየውም ልክ እንደ ስሙ ነው፤ ሞኝነትም ዐብሮት የኖረ ነው። እኔ አገልጋይህ ግን ጌታዬ የላካቸውን ጕልማሶች አላየኋቸውም።