ምሳሌ 12:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት፤ አሳፋሪ ሚስት ግን ዐጥንቱ ውስጥ እንዳለ ንቅዘት ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጐበዝ ሴት ለባሏ ዘውድ ናት፥ አሳፋሪ ሴት ግን በአጥንቱ ውስጥ እንደ ቅንቅን ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አስተዋይ ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤ ባልዋን የምታሳፍር ሴት ግን አጥንትን እንደሚያደቅ በሽታ ናት። እንደሚጐዳ ነቀርሳ በሽታ ትሆንበታለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤ ክፉ ሴት ግን ነቀዝ እንጨትን እንደሚበላ እንዲዚሁ ባሏን ትጐዳለች። |
እኔ ሰማሁ፤ ልቤም ደነገጠብኝ፤ ከንፈሬ ከድምፁ የተነሣ ተንቀጠቀጠ፤ ፍርሀት እስከ ዐጥንቴ ዘልቆ ገባ፤ እግሬም ተብረከረከ፤ ሆኖም በሚወርረን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፣ የጥፋትን ቀን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።