ምሳሌ 11:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልበ ቢስ ባልንጀራውን ያንኳስሳል፤ አስተዋይ ግን አንደበቱን ይገዛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዳጁን የሚንቅ ልበ ጐደሎ ነው፥ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በንቀት ተናግሮ ሰውን የሚያዋርድ፥ ማስተዋል የጐደለው ነው፤ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥበብ የጐደለው የሀገሩን ሰው ይንቃል። ብልህ ሰው ግን ጸጥታን ያመጣል። |
ከዚያም ዜቡል፣ “እንገዛለት ዘንድ አቢሜሌክ ማን ነው? ብለህ የደነፋኸው አሁን የት አለ? ያቃለልሀቸውስ ሰዎች እነዚህ አይደሉምን? በል ውጣና ግጠማቸው” አለው።
አንዳንድ ምናምንቴ ሰዎች ግን፣ “እንዲህ ያለ ሰው እንዴት ሊያድነን ይችላል?” በማለት ናቁት፤ ስጦታም አላመጡለትም። ሳኦል ግን ዝም አለ።