ምሳሌ 1:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን በተጣራሁ ጊዜ እንቢ ስላላችሁኝ፣ እጄንም ስዘረጋ ማንም ግድ ስላልነበረው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጠራሁ ጊዜ እምቢ ስላላችሁ፥ እጄን በዘረጋሁ ጊዜ ማንም ስላላስተዋለ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እኔ እንድትመጡ እጄን ዘርግቼ ጠራኋችሁ፤ እናንተ ግን ጥሪዬን አልተቀበላችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጠራሁ ጊዜ አልሰማችሁኝምና እጄን ዘረጋሁ፥ ማንም አላስተዋለም ነገርንም አበዛሁ፥ አልመለሳችሁልኝም፥ |
እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነሣሣና ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ላይ ተሣለቁ፤ ቃሉን ናቁ፤ ነቢያቱንም አቃለሉ።
በመጣሁ ጊዜ ለምን በዚያ ሰው አልነበረም? በተጣራሁስ ጊዜ የሚመልስ ሰው እንዴት በዚያ ታጣ? ስለ እናንተ ወጆ ለመክፈል ክንዴ ዐጥራ ነበርን? እናንተንስ ለማዳን ኀይል አነሰኝን? እነሆ፤ በተግሣጼ ባሕሩን አደርቃለሁ፤ ወንዞችን ምድረ በዳ አደርጋለሁ፤ ዓሦቻቸው ውሃ በማጣት ይሸታሉ፤ በጥማትም ይሞታሉ።
ተጣርቼ ስላልመለሳችሁ፣ ተናግሬ ስላልሰማችሁ፣ በፊቴ ክፉ ነገር ስላደረጋችሁ፣ የሚያስከፋኝን ነገር ስለ መረጣችሁ፣ ለሰይፍ እዳርጋችኋለሁ፤ ሁላችሁም ለመታረድ ትጐነበሳላችሁ።”
ለዐመፀኛ ሕዝብ፣ መልካም ባልሆኑ መንገዶች ለሚሄዱ፣ የልባቸውን ምኞት ለሚከተሉ፣ ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ። ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝቦች፣
ስለዚህ ችግር እንዲደርስባቸው አደርጋለሁ፤ የፈሩትንም አመጣባቸዋለሁ፤ በተጣራሁ ጊዜ የመለሰ፣ በተናገርሁ ጊዜ ያደመጠ ሰው የለምና። በፊቴ ክፉ ነገር አደረጉ፤ የሚያስከፋኝንም መረጡ።”
“ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ሁሉ ላይ አደርሳለሁ ያልሁትን ጥፋት ሁሉ አመጣባቸዋለሁ፤ በተናገርኋቸው ጊዜ፣ አልሰሙኝምና በጠራኋቸውም ጊዜ አልመለሱልኝም።’ ”