ዘኍል 7:78 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዐሥራ ሁለተኛው ቀን የንፍታሌም ሕዝብ አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ ስጦታውን አመጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓሥራ ሁለተኛውም ቀን የንፍታሌም ልጆች አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ አቀረበ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዐሥራ ሁለተኛው ቀን መባውን ያቀረበው ከንፍታሌም ነገድ የዔናን ልጅ አሒራዕ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዐሥራ ሁለተኛውም ቀን የንፍታሌም ልጆች አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ መባውን አቀረበ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአሥራ ሁለተኛውም ቀን የንፍታሌም ልጆች አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ፤ |
እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ ዐምስት አውራ በግ፣ ዐምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው ዐምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የኤክራን ልጅ ፋግኤል ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።