ዘኍል 7:54 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በስምንተኛው ቀን የምናሴ ሕዝብ አለቃ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ስጦታውን አመጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በስምንተኛውም ቀን የምናሴ ልጆች አለቃ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል አቀረበ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስምንተኛው ቀን መባውን ያቀረበው ከምናሴ ነገድ የፍዳጹር ልጅ ገማልኤል ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስምንተኛውም ቀን የምናሴ ልጆች አለቃ የፈዳሱር ልጅ ገማልያል መባውን አቀረበ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስምንተኛውም ቀን የምናሴ ልጆች አለቃ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል፤ |
እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ ዐምስት አውራ በግ፣ ዐምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው ዐምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።
ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣