ዘኍል 7:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአራተኛው ቀን የሮቤል ሕዝብ አለቃ የስዲዮር ልጅ ኤሊሱር ስጦታውን አመጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአራተኛውም ቀን የሮቤል ልጆች አለቃ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር አቀረበ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአራተኛው ቀን መባውን ያቀረበው ከሮቤል ነገድ የሰድዩር ልጅ ኤልጹር ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአራተኛውም ቀን የሮቤል ልጆች አለቃ የሴድዮር ልጅ ኤሊሱር መባውን አቀረበ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአራተኛውም ቀን የሮቤል ልጆች አለቃ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር፤ |
እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ ዐምስት አውራ በግ፣ ዐምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው ዐምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የኬሎን ልጅ ኤልያብ ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።
ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣