ዘኍል 6:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከዚያም ናዝራዊው ተስሎ የተለየበትን ጠጕር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይላጨው፤ ጠጕሩንም ወስዶ ከኅብረቱ መሥዋዕት ሥር በሚነድደው እሳት ውስጥ ይጨምረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናዝራዊውም የተቀደሰውን የራሱን ጠጉር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይላጫል፥ የተቀደሰውንም ራስ ጠጉር ወስዶ ከአንድነት መሥዋዕት በታች ወዳለው እሳት ይጥለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመገናኛው ድንኳን በር መግቢያ ላይ ናዝራዊው ጠጒሩን ላጭቶ የአንድነት መሥዋዕት በሚቃጠልበት እሳት ላይ ያኖረዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተሳለውም የተሳለውን የራስ ጠጕር በምስክሩ ድንኳን አጠገብ ይላጫል፤ የስእለቱንም ራስ ጠጕር ወስዶ ከደኅንነት መሥዋዕት በታች ወዳለው እሳት ይጥለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናዝራዊውም የተለየውን የራሱን ጠጕር በመገናኛው ድንኳን አጠገብ ይላጫል፥ የመለየቱንም ራስ ጠጕር ወስዶ ከደኅንነት መሥዋዕት በታች ወዳለው እሳት ይጥለዋል። |
“ ‘ስእለት ተስሎ ራሱን በለየበት ጊዜ ሁሉ ምላጭ ራሱን አይንካው፤ ለእግዚአብሔር የተለየበት ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ የተቀደሰ ይሁን፤ የራስ ጠጕሩንም ያሳድግ።
ከዚህ በኋላ ጳውሎስ ብዙ ቀን በቆሮንቶስ ተቀመጠ፤ ከዚያም ወንድሞችን ተሰናብቶ ከጵርስቅላና ከአቂላ ጋራ በመርከብ ወደ ሶርያ ሄደ። ስእለትም ስለ ነበረበት ክንክራኦስ በተባለ ቦታ ራሱን ተላጨ።
እነዚህን ሰዎች ይዘህ ከእነርሱ ጋራ የመንጻቱን ሥርዐት ፈጽም፤ ራሳቸውንም እንዲላጩ የሚጠየቀውን ገንዘቡን ክፈልላቸው፤ በዚህም ስለ አንተ የተነገራቸው ሰዎች ሁሉ የሰሙት እውነት እንዳልሆነና አንተ ራስህ ሕጉን ጠብቀህ የምትኖር መሆንህን ያውቃሉ።
ጳውሎስም በማግስቱም ሰዎቹን ይዞ ሄደ፤ ዐብሯቸውም የመንጻቱን ሥርዐት ፈጸመ። ከዚያም የመንጻቱ ሥርዐት መቼ እንደሚያበቃና የእያንዳንዳቸውም መሥዋዕት መቼ እንደሚቀርብ ለማስታወቅ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ።