ዘኍል 4:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሜራሪያውያንን በየጐሣቸውና በየቤተ ሰቦቻቸው ቍጠራቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የሜራሪንም ልጆች በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸውም ቤቶች ቁጠራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሜራሪ ዘሮች የሆኑትን ሌዋውያን በየትውልዳቸው፥ በየቤተሰባቸው ቊጠራቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሜራሪንም ልጆች በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸውም ቤቶች ቍጠራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሜራሪንም ልጆች በየወገናቸው በየአባቶቻቸውም ቤቶች ቍጠራቸው። |
እንግዲህ የጌርሶናውያን ጐሣዎች በመገናኛው ድንኳን የሚኖራቸው አገልግሎት ይህ ነው፤ ተግባራቸውም በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር አመራር ሥር ይሆናል።
ለሜራሪያውያንም ለአገልግሎታቸው በሚያስፈልጋቸው መጠን አራት ሠረገሎችና ስምንት በሬዎች ሰጠ። እንግዲህ እነዚህ ሁሉ በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር ኀላፊነት የሚመሩ ነበሩ።