ከእነርሱም አንዳንዶቹ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በኀላፊነት ይጠብቁ ነበር፤ ዕቃዎቹም በሚገቡበትና በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ ይቈጥሩ ነበር።
ዘኍል 4:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንዲሁም በመቅደሱ ውስጥ ለአገልግሎት የሚሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ ወስደው በሰማያዊ ጨርቅ በአቆስጣ ቍርበት በመሸፈን በመሸከሚያው ሳንቃ ላይ ያስቀምጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመቅደስም ውስጥ የሚገለገሉባቸውን የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ይውሰዱ፥ በሰማያዊውም መጐናጸፊያ ውስጥ ያስቀምጡአቸው፥ በአቆስጣም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑአቸው፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመቅደሱ መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች ሁሉ ወስደው በሰማያዊ ጨርቅ ይሸፍኑአቸው፤ የለፋ ስስ ቊርበት ደርበውም በመሸከሚያው ተራዳ ላይ ያኑሩአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመቅደስም ውስጥ የሚያገለግሉበትን የማገልገያውን ዕቃ ሁሉ ይውሰዱ፤ በሰማያዊዉም መጐናጸፊያ ውስጥ ያስቀምጡት፤ በአቆስጣም ቍርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፤ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመቅደስም ውስጥ የሚያገልግሉበትን የማገልገያውን ዕቃ ሁሉ ይውሰዱ፥ በሰማያዊውም መጐናጸፊያ ውስጥ ያስቀምጡት፥ በአቆስጣም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉት። |
ከእነርሱም አንዳንዶቹ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በኀላፊነት ይጠብቁ ነበር፤ ዕቃዎቹም በሚገቡበትና በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ ይቈጥሩ ነበር።
ሌሎቹ ሌዋውያን ደግሞ ዕቃዎቹንና የቤተ መቅደሱን ንዋያተ ቅድሳት፣ ዱቄቱን፣ የወይን ጠጁን፣ የወይራ ዘይቱን፣ ዕጣኑን፣ የሽቱውን ቅመማ ቅመም እንዲጠብቁ ተመድበው ነበር።
ኪራምም ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን ሠራ። ኪራምም ለአምላክ ቤተ መቅደስ አገልግሎት ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራውን ሥራ ፈጸመ እነዚህም፦
ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ሜንጦዎችንና ከእነዚሁም ጋራ የተያያዙ ዕቃዎች። ኪራምአቢ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ እንዲሆኑ ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራለት ከሚብረቀረቅ ናስ ነበር።
ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ የመብራት መኰስተሪያዎች፣ ለመርጨት የሚያገለግሉ ጐድጓዳ ሳሕኖች፣ ጭልፋዎችና ጥናዎች፣ እንደዚሁም የቤተ መቅደሱ የወርቅ መዝጊያዎች፣ ይኸውም የቅድስተ ቅዱሳኑ የውስጠኛው መዝጊያዎችና የቤተ መቅደሱ አዳራሽ መዝጊያዎች ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ።
“በገጸ ኅብስቱ ገበታ ላይ ሰማያዊ ጨርቅ ይዘርጉበት፤ በላዩም ላይ ወጭቶች፣ ጭልፋዎች፣ ጽዋዎች፣ ለመጠጥ ቍርባን የሚሆኑትን ማንቈርቈሪያዎች እንዲሁም ሁልጊዜ ከዚያ የማይታጣውን ኅብስት ያስቀምጡ።
“ደግሞም ሰማያዊ ጨርቅ ወስደው ማብሪያ መቅረዙንና መብራቶቹን፣ መኰስተሪያዎቹንና የኵስታሪ መቀበያዎቹን፣ እንዲሁም ለዚሁ አገልግሎት የሚውሉትን የዘይት ዕቃዎች ይሸፍኑበት።