ሞዓባውያንም የምድያምን ሽማግሌዎች፣ “በሬ የመስክ ሣር ጠራርጎ እንደሚበላ ሁሉ፣ ይህም ሰራዊት በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ጠራርጎ የሚያጠፋ ነው” አሏቸው። ስለዚህ በዚያ ጊዜ የሞዓብ ንጉሥ የነበረው የሴፎር ልጅ ባላቅ፣
ዘኍል 25:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ምድያማውያንን እንደ ጠላት ቈጥራችሁ ፍጇቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ምድያማውያን እንደ ጠላት ቁጠሩአቸው እነርሱንም ድል ንሱአቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በምድያማውያን ላይ አደጋ ጥላችሁ ደምስሱአቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድያማውያንን አስጨንቋቸው፤ ግደሉአቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፌጎር በመቅሠፍቱ ቀን ስለተገደለችው ስለ ምድያም አለቃ ልጅ ስለ እኅታቸው ስለ ከስቢ በፌጎር ምክንያት በሸነገሉአችሁ ሽንገላ አስጨንቀዋችኋልና ምድያማውያንን አስጨንቁአቸው ግደሉአቸውም። |
ሞዓባውያንም የምድያምን ሽማግሌዎች፣ “በሬ የመስክ ሣር ጠራርጎ እንደሚበላ ሁሉ፣ ይህም ሰራዊት በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ጠራርጎ የሚያጠፋ ነው” አሏቸው። ስለዚህ በዚያ ጊዜ የሞዓብ ንጉሥ የነበረው የሴፎር ልጅ ባላቅ፣
ይኸውም ፌጎር ላይ በተፈጸመው ድርጊትና በፌጎር ምክንያት በመጣው መቅሠፍት በተገደለችው በምድያማዊው አለቃ ልጅ፣ በእኅታቸው በከስቢ አታልለው የጠላትነት ሥራ ስለ ሠሩባችሁ ነው።”
እንደ ገና እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ እግዚአብሔርም ለምድያማውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ሰባት ዓመት ገዟቸው።