ሰዎች ወርቅ ከከረጢታቸው ይዘረግፋሉ፤ ብርንም በሚዛን ይመዝናሉ፤ አንጥረኛን ይቀጥራሉ፤ እርሱም አምላክ አድርጎ ያበጅላቸዋል። እነርሱም ይሰግዱለታል፤ ያመልኩታልም።
ዘኍል 23:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም በፈስጋ ተራራ ጫፍ ላይ ወዳለው ወደ ጾፊም ሜዳ ወሰደው፤ እዚያም ሰባት መሠዊያ ሠርቶ በእያንዳንዱ ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ ሠዋ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ጾፊምም ሜዳ ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ ላይ ወሰደው፤ ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን አንድም አውራ በግ አሳረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በፒስጋ ተራራ ጫፍ ላይ ወደሚገኘው ወደ ጾፊም መስክ ወሰደው፤ እዚያም ሰባት መሠዊያዎችን ሠርቶ በእያንዳንዱ ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ ሠዋ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሜዳ ወደ ተገነባ ግንብ ራስ ላይም ወሰደው፤ አዞረውም፤ ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፤ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን፥ አንድም አውራ በግ አሳረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ጾፊምም ሜዳ ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ ላይ ወሰደው፤ ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን አንድም አውራ በግ አሳረገ። |
ሰዎች ወርቅ ከከረጢታቸው ይዘረግፋሉ፤ ብርንም በሚዛን ይመዝናሉ፤ አንጥረኛን ይቀጥራሉ፤ እርሱም አምላክ አድርጎ ያበጅላቸዋል። እነርሱም ይሰግዱለታል፤ ያመልኩታልም።
ገለዓድ ክፉ ነው? ሕዝቡም ከንቱ ናቸው! ኰርማዎችን በጌልገላ ይሠዋሉን? መሠዊያዎቻቸው በታረሰ መሬት ላይ እንዳለ፣ የድንጋይ ክምር ይሆናሉ።
ከዚህ በኋላ ባላቅ፣ “እነርሱን ማየት ወደምትችልበት ወደ ሌላ ቦታ እንሂድ፤ በእዚያም ሁሉን ሳይሆን በከፊል ብቻ ታያቸዋለህ፤ እዚያም ሆነህ እነርሱን ርገምልኝ” አለው።
ወደ ፈስጋ ተራራ ጫፍ ውጣ፤ ወደ ምዕራብና ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅም ተመልከት። አንተ ዮርዳኖስን ስለማትሻገር፣ ምድሪቱን በዐይንህ ብቻ እያት።
ሙሴ ከሞዓብ ሜዳ ተነሥቶ ለኢያሪኮ ትይዩ ወደ ሆነው ፈስጋ ጫፍ፣ ወደ ናባው ተራራ ወጣ። በዚያም እግዚአብሔር ምድሪቱን ሁሉ አሳየው፤ ይኸውም ከገለዓድ እስከ ዳን፣