ዘኍል 23:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የያዕቆብን ትቢያ ማን ቈጥሮ ይዘልቃል? የእስራኤልንስ ሩብ ማን ይቈጥረዋል። የጻድቁን ሞት እኔ ልሙት፤ ፍጻሜዬም የርሱ ዐይነት ፍጻሜ ትሁን!” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የያዕቆብን ትቢያ ማን ይቈጥራል? የእስራኤልስ አራተኛውን ክፍል ማን ይቈጥራል? የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት፥ ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ትቢያ ብዛት ያላቸውን የያዕቆብ ዘሮች ማን ሊቈጥር ይችላል ወይስ እንደ አዋራ ብናኝ ብዛት ያለውን የእስራኤልን ሩብ ብዛት ማን ሊገምት ይችላል? የጻድቃንን ሞት እንድሞት አድርገኝ መጨረሻዬንም እንደ እነርሱ አድርገው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የያዕቆብን ዘር ማን ያውቀዋል? የእስራኤልንስ ሕዝብ ማን ይቈጥረዋል? ሰውነቴም ከጻድቃን ሰውነት ጋር ትሙት፤ ዘሬም እንደ እነርሱ ዘር ትሁን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የያዕቆብን ትቢያ ማን ይቈጥራል? የእስራኤልስ እርቦ ማን ይቈጥራል? የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት፥ ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን። |
ዘርህ እንደ ምድር አሸዋ ይበዛል፤ በምዕራብና በምሥራቅ፣ በሰሜንና በደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በአንተና በዘርህ አማካይነት ይባረካሉ።
በየሰራዊታቸው ሆነው ከሮቤል ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ አንድ መቶ ዐምሳ አንድ ሺሕ አራት መቶ ዐምሳ ናቸው፤ እነዚህ ቀጥለው ይመጣሉ።
በየሰራዊታቸው ሆነው ከዳን ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች ሁሉ አንድ መቶ ዐምሳ ሰባት ሺሕ ስድስት መቶ ናቸው፤ እነርሱም በዐርማቸው ሥር በመጨረሻ ይመጣሉ።
መኖሪያችን የሆነው ምድራዊ ድንኳን ቢፈርስም፣ በሰው እጅ ያልተሠራ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የሆነ ዘላለማዊ ቤት በሰማይ እንዳለን እናውቃለን።
ከዚያም፣ “ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ ሆነው የሚሞቱ ብፁዓን ናቸው ብለህ ጻፍ” የሚል ድምፅ ከሰማይ ሰማሁ። መንፈስም፣ “አዎ፣ ሥራቸው ስለሚከተላቸው ከድካማቸው ያርፋሉ” ይላል።